August 24, 2026
ተደራሽ በቅርቡ ህብረት ስራ ማህበሩን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሰራተኖች አቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና አራት ኪሎ በሚገኘው ዋና ቢሮ እየሰጠ ይገኛል፡፡ ስለጠናው ከዛሬ ነሃሴ 18 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ በመክፈቻው ቀን ስልጠናውን የሰጡት የተደራሽ አብይ ቅርጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ዳዊት ናቸው ፡፡ ስራ አስኪያጁ አዲስ ቅጥር ለፈፀሙ ሰራተኞች ስለቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር አስቀድመው ገለፃ አድርገዋል፡፡ ህብረት ስራ ማህበራት ለህበረተሰቡ ስለሚሰጡት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያነሱት ስራ አስኪያጁ መባስከተልም ተደራሽ በዋነኝነት ስለሚሰጠው የቁጠባና ብድር አገልግሎት በሰፊው ገለፃ አድርገዋል ፡፡ የተደራሽ አገልግሎትን ፈልጎ የመጣ አባል በምን መልኩ መስተናገድ እንደሚገባውና የደንበኛ አያያዝ ምን ሊመስል እንደሚችል በሰፊው አብራርተዋል፡፡ በማስከተልም በተደራሽ ቤት ስላሉ ውስጣዊ አሰራሮች አዲስ ቅጥር ለፈፀሙት ሰራተኞች ሰፊ ገለፃ ከተሰጠበት በኀላ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በሰራተኞች በኩልም ግልፅ ባልሆኑላቸው ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ጥቄዎችን ያነሱ ሲሆን በስራ አስኪያጁ በኩል ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡ ስልጣው በቀሩት ቀናት በቡድን ስራ፣በሰራተኛ ስነምግባር እንዲሁም በሲስተም አያያዝ ላይ እንሰሚያተኩር ተገልጿል።